የብሪታኒያ የፓርላማ አባላት ና ብሪታኒያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ስለ መገናኛ ብዙሀን አፈና እና በቅርቡ ስለ ሚደረገው ምርጫ ባለፈው ሰኞ በብሪታኒያ ፓርላማ ውስጥ ውይይት አካሂደዋል ።
ጽህፈት ቤቱ ብሪታኒያ በሚገኘው የሶስተኛው ዓለም ሀገሮች የጋራ ስምምነት በተሰኘው ዓለም ዓቀፍ ድርጅት አማካይነት በተዘጋጀው በዚህ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት እንደሚረገጥ ነፃ የመገናኛ ብዙሀን እንደሌለ ተነስቷል ። በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ አለመኖሩን የሚያውቀው ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብም ከመንግስት ጎን እንዳይቆም ተጠይቋል ።
ሃና ደምሴ፤ ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ